ዛሬ ማክሰኞ እንደአውሮፓውያን የዘመን ኣቆጣጠር ህዳር አስራ አንድ ቀን በየዓመቱ ሀገራቸውን በውትድርና ያገለገሉ እና መስዋዕትነት የከፈሉላት ወንዶችና ሴቶች የሚከበሩበት ዕለት ነው።
ታዲያ ዩናይትድ ስቴትስን በውትድርና ያገለገሉዋት አርበኞችዋ ዜጎችዋ ብቻ ኣይደሉም። .
በጦር ሃይሎች አገልግሎቱ ለመግባት የአሜሪካ ዜጋ ባይሆኑም ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ግሪን ካርድ በሚባለው ማመልከት እንዲቻል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ተፈቅዱዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር መዝገብ መሰረት ጦር ሃይሎችዋ ውስጥ ግዳጅ ላይ ያሉ ከስድሳ ኣምስት ሺህ በላይ እና የውጭ ሃገር ተወላጆች አሉ።
የቪኦኤዋ Deborah Block በዋሽንግተን ኣካባቢ የሚኖሩ ኣንድ የሶማሊያ ኣንድ የፊሊፒንስ ተወላጅ ኣነጋግራ “ኣሜሪካ ጦር ሰራዊት ውስጥ ገብታችሁ ህይወታችሁን ለኣደጋ ማጋለጥን እንዴት ልትወስኑ ቻላችሁ?” ብላ ጠይቃቸዋለች። ሙሉ ዘገባውን ከዚህ ያድምጡ