በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መርከቦች በየመን የባህር ዳርቻ የሚሳዬል ጥቃት ደረሰባቸው


የመን
የመን

በየመን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ የባብ አል ማንዴብ ሰርጥን ሲያቋርጥ የነበረ አንድ መርከብ ዛሬ ሰኞ የሚሳዬል ጥቃት ደርሶበታል ሲሉ የደህንነት ተቋማት አስታወቁ፡፡

ዛሬ እኩለ ሌሊት ላይ ተፈጽሟል የተባለው ጥቃት የሁቲ አማፅያን ባለፉት ወራት በቀይ ባህር መርከቦች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን የሰነዘሩበት አካባቢ ነው ሲል እንግሊዝ የባህር ንግድ አገልግሎት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል።

ድርጅቱ ጨምሮ እንዳስታወቀው “የመርከቢቱ ሠራተኞቹ ደህና ናቸው መርከቧም ወደ ሚቀጥለው ወደብ የምታደርገው ጉዞዋን ቀጥላለች” ብሏል፡፡

አምብሬይ የተባለው ሌላዉ የደህንነት ድርጅት ንብረትነቷ የግሪክ የሆነችና የማርሻል ደሴቶችን አርማ ያውለበለበች የጭነት መርከብ፣ “በ20 ደቂቃዎች ውስጥ ሁለት ጊዜ የሚሳዬል ጥቃት ኢላማዎች ሆናለች ” ሲል ገልጾ በአንደኛው ጎኗ አካላዊ ጉዳት የደረሰባት መሆኑንም አስታውቋል፡፡

መርከቧ የታጠቁ የግል ጠባቂ ቡድኖች እንደነበሯትም አምብሬይ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

ፀረ-ምዕራባውያን ፀረ እስራኤል አቋም ያላቸው በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች በቀይ ባህር ላይ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ለወራት ሲያደርሱት የቆየው ጥቃት የዩናትድ ስቴትስ እና የእንግሊዝን የአጸፋ ጥቃቶች አስከትለዋል፡፡

የጥቃቶቹ ኢላማ ካላፈው ጥቅምት ጀምሮ በተባባሰው የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት በጋዛ ለሚገኙ ፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት የሚደረጉ መሆኑን አማጽያኑ ይናገራሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG