በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቬኔዙዌላ መንግሥትና የተቃዋሚ ጥምረት ተወካዮች የሀገሪቱ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳይ ላይ

የቬኔዙዌላ መንግሥትና የተቃዋሚ ጥምረት ተወካዮች፣ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለማስወገድ በሚረዳ የመፍትሔ ሃሳብ ላይ ለመወያየት ዛሬ አርብ ዶምኒካ ሪፖብሊክ ውስጥ እንደሚሰባሰቡ ተገለፀ።

የቬኔዙዌላ መንግሥትና የተቃዋሚ ጥምረት ተወካዮች፣ የሀገሪቱን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ለማስወገድ በሚረዳ የመፍትሔ ሃሳብ ላይ ለመወያየት ዛሬ አርብ ዶምኒካ ሪፖብሊክ ውስጥ እንደሚሰባሰቡ ተገለፀ።

ሳንታ ዶሚንጎ በሚገኘው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥ የሚሰባሰቡት የሁለቱም ወገኖች ተወካዮች፣ የዛሬ ውይይታቸውን፣ ከሁለት ሳምንታት በፊት ካቆሙበት እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

ተቃዋሚው የዴሞክራቲክ ሕብረት ለውይይት ያቀረባቸው ነጥቦች፣ ነፃና ተዓማኒ የምርጫ ሂደት፣ የታሰሩ የተቃዋሚ አባላት መለቀቅ፣ የብሔራዊ ምክር ቤቱ ሙሉ ሥልጣን መመለስ፣ ረሀብ ላጠቃቸው አካባቢዎች የምግብ ማስተላለፊያ ኮሪዶር እንዲከፈትና የተሟላ የህክምና አገልግሎት የሚሉትን ያካትታሉ።

የፕሬዚደንት ኒኮላስ ማዱሮን አስተዳደር የተወከሉ ልዑካን፣ ሀገሪቱ ላይ የተጣለው ዓለማቀፍ ማዕቀብ እንዲነሳ ይጠይቃሉም ተብሏል።

የፕሬዚደንት ማዱሮ አመራር ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰርት ጫና ለመፍጠር፣ ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮፓ ሕብረትም የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣላቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG