በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቬነዝዌላ ወታደሮች የድንበር መተላለፊያ በር ዘጉ


የቬነዝዌላ ወታደሮች ከዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ሃገሮች የሚላከውን ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማገድ - ቁልፍ የድንበር መተላለፊያ በር ዘግተዋል።

በትላንትናው ዕለትም ቬነዝዌላን ከኮሎምቢያ በሚያገናኘው ድልድይ መሃል - ግዙፍ ብርቱካንማ ቀለም ያለው ነዳጅ ጫኝ መርከብና ሁለት ሰማያዊ ኮንቴነሮችን አኑረዋል። የታጠቁ ወታደሮች ደግሞ ድንበሩን ለመሻገር የሚሞክሩትን እንዲመልሱ አካባቢውን ይቃኛሉ።

ዩናይትድ ስቴትስ በአስቸኳይ ያስፈልጋሉ የተባሉትን ምግብና መድሃኒት ጨምሮ ለቬነዝዌላ $20 ሚሊዮን ዶላር ለመርዳት ቃል ገብታለች። ፕሬዘዳንቱ ኒኮላስ ማዱሮ ግን “ቬነዝዌላ የለማኞች ሃገር አይደለችም - ለዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ወረራም መንገዱን አትጠርግም” ሲሉ ተከራክረው ዕርዳታውን ውድቅ አድርገዋል።

በነዳጅ ዘይት ሽያጭ የሚታገዘው የቬነዝዌላ ምጣኔ ኃብት - የዓለም ገበያ በመውደቁ በሙስናና በሶሺያሊስቱ ፖሊሲዎች ምክንያት ተንኮታክቷል። በዚህም ሳቢያ ሃገሪቱ ውስጥ የምግብ የነዳጅ ዘይትና ሌሎች መሠረታዊ ቁሳቁሶች ክፍተኛ እጥረት ተፈጥሯል። ግሽበት ከቁጥጥር ውጭ በመውጣቱም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቬነዝዌላ ዜጎች ወደ ጎረቤት ኮሉምቢያ መኮብለል ተገደዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG