በትናንትናው ዕለት በኔቫዳ ዩኒቨርስቲ፣ ላስ ቬጋስ፣ ተኩስ በመክፈት ሶስት ሰዎችን የገደለው ታጣቂ በቅርቡ በአስተማሪነት ለመቀጠር ያመለከተና ያልተሳካለት ፕሮፌሰር እንደነበር ተዘግቧል።
ግለሰቡ ከፖሊስ ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ እንደተገደለም ለማወቅ ተችሏል።
አንድ አራተኛ ግለሰብም ለሕይወት አስጊ ግን የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝም ታውቋል።
ዩኒቨርስቲው የሚገኘው ከቱሪስት መናኽሪያ ከሆነው እና ከስድስት ዓመታት በፊት በአሜሪካ ታሪክ አስከፊ የጅምላ ግድያ ከተፈጸመበት የላስ ቬጋስ መንደር ሶስት ኪ.ሜ. ያህል ርቀት ላይ እንደሆነ ታውቋል። ከአስከፊው ቀን የተገኘው ልምድ የትናንቱን ጥቃት በአጭሩ ለመቅጨት እንዳስቻለ ፖሊስ ገልጿል።
ጥቃት አድራሹ በዩኒቨርስቲው ሕንጻ መተላለፊያዎች እየተዘዋወረ ሲተኩስ፣ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች ራሳቸውን በክፍል ውስጥ እና በተማሪዎች መኖሪያ ክፍሎች ለመደበቅ ተገድደዋል።
ግለሰቡ ለማስተማር ሥራ ማመልከቻ አስገብቶ ሳይሳካለት የቀረ እንደነበር ተመልክቷል።
መድረክ / ፎረም