በርካታ አሜሪካውያን የፍቅር ቀን ገበያቸውን የሚያከናውኑት በመጨረሻ ሰዓት ላይ ነው። በመጨረሻ ሰዓት መገበያየት ደግሞ፣ ብዙ ያስከፍላል።
‘ብሔራዊ የችርቻሮ ፌዴሬሽን’ እንደሚለው፣ በመጨረሻው ሠዓት በሚደረግ ግብይት፣ አሜሪካኖቹ ለዛሬው የፍቅር ቀን 25.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያወጡ ይጠበቃል። ዋናው ተሸማቹ ሸቀጥ ከረሜላ እንደሆነ ተነግሯል።
‘ኑመሬተር’ የተሰኘ የገበያ አጥኚ ኩባንያ በበኩሉ እንደሚለው ደግሞ፤ ለአበባ፣ ለከረሜላና ለፍቅር መግለጫ ካርዶች ገንዘብ የሚወጣው ከቀኑ ቀደም ብሎ ባሉት ሶስት ቀናትና በዋናው ቀን ቢሆንም፣ ሽያጩ ከፍተኛ የሚሆነው ግን በፍቅር ቀን፣ በዕለቱ ነው።
ክሮገር፣ ታርጌት፣ ዋልግሪንስና ዋልማርት የመሰሉ የአሜሪካ የሸቀጥ መደብሮች፣ በመጨረሻው ሰዓት የሚደረገው ግብይት ከሳምንቱ ሽያጫቸው ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ይገልጻሉ።
ፍቅርን ለመግለጽ ቀኑን መጠበቅ አያስፈልግም፣ ፍቅርን በዓመት አንዴ ሳይሆን፣ በየቀኑ ማክበር አለብን”
ሸቀጦቹን በየቤቱ የሚያደርሱ የትራንስፖርት ኩባያዎችም በመጨረሻው ቀን የሚደረገው ግብይት ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ያስታውቃሉ። ኡበር እንደሚለው የአበባ ትዕዛዝ የሚደርሰው በዕለቱ ከጠዋቱ አራት ሰዐት እስከ ከሰዓት በኋላ 11 ሰዓት እንደሆነ ገልጿል። የአበባው ዋጋ በማግስቱ ከሚኖረው ጋር ሲነጻጸር 60 በመቶ ጭማሪ አለው ብሏል።
የፍቅር ቀን ከገና በኋላ መምጣቱ ሌላው ችግር ነው የሚሉት የስነልቦና ባለሙያዎች፣ በገና ገበያ ምክንያት ኪሱ የሳሳ ገበያተኛ፣ ለፍቅር ቀን ወጪ ሲያመነታ ቀኑ ይደርሳል ብለዋል።
“ፍቅርን ለመግለጽ ቀኑን መጠበቅ አያስፈልግም፣ ፍቅርን በዓመት አንዴ ሳይሆን፣ በየቀኑ ማክበር አለብን” ሲሉም ምክራቸውን ለግሰዋል።
መድረክ / ፎረም