ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዛዳንት ዶናልድ ትረምፕ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና የሜክሲኮው ፕሬዘዳንት ኤንሪኬ ቴኛ ኒኤቶ “ናፍታ” በመባል የሚታወቀውን የሰሜን አሜሪካ ነፃ የንግድ ሥምምነት የሚተካ አዲስ ሥምምነት ዛሬ ተፈራርመዋል።
ይህ አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ፣ ሜክሲኮና ካናዳ ሥምምነት የተፈረመው ከትላንት ጀምሮ በአርጀንቲና ከተማ በቦነስ አይሬስ እየተካሄደ ካለው ከጂ-20 የመሪዎች ጉባዔ ጎን ነው።
ጉባዔውን በመከታተል ላይ ያለችው ባልደረባችን ግሬታ ቫንስ ስተርን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትረምፕን በሥምምነቱ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አነጋግራለች።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ