ሁሴን ቦልት በኪንግስተን ጃማይካ ብሔራዊ ስታድዮም ከነሐስ የተሠራ ሥምንት ጫማ ርዝመት ያለው ሃውልት ቆመለት፡፡
ለሁሴን ቦልት በብሔራዊ ስታድየም የቆመለትን ግዙፍ ኃውልት የቀረፀው ታዋቂው ባሲል ዋትሶን ነው፡፡
የቦልትን በዓለም የታወቀበትን ምልክቱን ያሳያል፡፡ የጃማይካው ፈጣን ሯጭ ለንደን ላይ ዘንድሮ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ፣ ራሱን ከውድድሮች ማግለሉ ይታወሳል፡፡
ደስታውን ለመግለጭ በኃውልቱ ምርቃ ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝቷል፡፡
“ለዚህ ታላቅ ክብር እደርሣለሁ ብዮ ፈፅሞ አላስብም ነበር ብሏል፡፡
ሥድስት ጊዜ በግሉ የኦሎምፒክ ወርቅ ያጠለቀውና፣ ሠባት የዓለም ሻምፒዮናነትን የተጎናፀፈው ተወዳጁ አትሌት ሁሴን ቦልት - ለዚህ ነው ሁልጊዜ ሰዎችን የማበረታታው፣ ምንም ሊደረስበት የማይቻል ነገር የለም ብሏል፡፡
የዓለምቀፍ አትሌቲክስ ፌደሬሽኖች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሴባስቲያን ኮበሥነ ሥርዓቱ ላይ በላኩት የቪድዮ መልዕክት
ቦልት ለአትሌቲክሱ ሩጫ ስፖርት ውድድር ያበረከተውን ከፍተኛ አስተዋፅዖ አውደሰዋል፡፡
“ገፅታውን ቀይሮታል፣ ሁሴን ቦልት ከትራኩ ዓለም መሰናበቱ ርግጥ ነው ከስፖርቱ ዓለም እንደማይርቅ ግን አምናለሁ” ሲሉም ሴባስቲያን አክለዋል፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ