በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩኤስኤአይዲ የዕርዳታ መጋዘኖች በህወሓት ታጣቂዎች መዘረፋቸውን አስታወቀ


በኢትዮጵያ የዩኤስኤአይዲ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ
በኢትዮጵያ የዩኤስኤአይዲ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ

የህወሓት ታጣቂዎች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሁሉ የዕርዳታ መጋዘኖችን መዝረፋቸውን ዩኤስኤአይዲ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የዩኤስኤአይዲ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ህወሓቶች በአማራ ክልል ውስጥ በገቡበት ከተማ ሁሉ መጋዘኖችን፣ የጭነት መኪናዎችን ዘርፈዋል፣ በደረሱባቸው መንደሮች ሁሉ ከፍተኛ ውድመት አስከትለዋል ብለዋል፡፡

ሾን ጆንስ በህወሓት ላይ ያቀረቡትን ይህን ክስ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ አጣጥለዋል፡፡ አቶ ጌታቸው ከሰዓታት በፊት በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ከመስመር ውጭ ስለሚሆኑ ተዋጊዎች ስለእያንዳንዱ ተቀባይነት የሌላው ባህሪ ማረጋገጥ ባንችልም፣ እንዲህ ዓይነቱ ዝርፊያ በዋነኝነት በአካባቢው ግለሰቦች እና ቡድኖች የተቀነባበረ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለን ያሉ ሲሆን ጉዳዩን በገለልተኛ ምርመራ እንደሚያጣሩትም ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ዩኤስኤአይዲ የዕርዳታ መጋዘኖች በህወሓት ታጣቂዎች መዘረፋቸውን አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00


XS
SM
MD
LG