በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት በመላው ዓለም የሚገኙ ሠራተኞቹን አሰናበተ


ዋሽንግተን የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት
ዋሽንግተን የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት

የትረምፕ አስተዳደር በመላው ዓለም የሚገኙ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት (ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ) ሠራተኞች ሥራ እንዲያቆሙ አዟል።

ላለፉት ስድሳ ዓመታት በመላው ዓለም ረሃብን በማስወገድ እና ለትምህርት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ በመስጠት የአሜሪካንን ደኅንነት ሲያስጠብቅ የከረመው ድርጅት የመዘጋት ዕጣ ገጥሞታል።

የትረምፕ አስተዳደር ለአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ድርጅት ሠራተኞች በኢሜይል በላከውና እና በድርጅቱ ድህረ ገጽ ላይ ባሠፈረው መልዕክት ነው ውሳኔውን ያስታወቀው።

የትረምፕ አስተዳደር ባለሥልጣኖች እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ የተቋቋመውንና ‘ዶጅ’ በመባል የሚታወቀውን ቡድን የሚመሩት ኢላን መስክ የዕርዳታ ድርጅቱ ለውጪ ሃገራት የሚያውለውን ገንዘብ እንደ ብክነት እንደሚቆጥሩት ተመልክቷል።

ትዕዛዙ ከዓርብ እኩለ ሌሊት በፊት ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ከሚፈለጉ ሠራተኞች ውጪ በመላው ዓለም የሚገኙ ሌሎች የድርጅቱ ሠራተኞች ወደ አሜሪካ ለመመለስ 30 ቀናት ተሰጥቷቸዋል።

ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ከሚፈለጉ ኮንትራክተሮች ውጪ ሥራቸውን እንዲያቆሙ እንደሚነገራቸውም ታውቋል።

የተቀረው የድርጅቱ ሥራም በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥር እንዲጠቃለል እንደሚደረግ ታውቋል።

ትረምፕ ለውጪ የሚሰጥ ርዳታ እንዲቆም ማድርጋቸውን ተከትሎ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ የድርጅቱ የሀገር ውስጥ ተቀጣሪዎች ተባረው ፕሮግራሞቹም እንዲቆሙ ተደርጓል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG