በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩኤስአይዲ በኢትዮጵያ በ90 ሚ. ዶላር ድጋፍ የሚተገብረውን የ“ዋሽ ፕሮጀክት” ይፋ አደረገ

ዩኤስአይዲ በኢትዮጵያ በ90 ሚ. ዶላር ድጋፍ የሚተገብረውን የ“ዋሽ ፕሮጀክት” ይፋ አደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:14 0:00

ዩኤስአይዲ በኢትዮጵያ በ90 ሚ. ዶላር ድጋፍ የሚተገብረውን የ“ዋሽ ፕሮጀክት” ይፋ አደረገ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ(USAID) በኩል የሚተገበሩ የ90 ሚሊዮን ዶላር ሁለት ፕሮጄክቶችን፣ ዛሬ ዐርብ ይፋ አደረገ፡፡

በንጹሕ መጠጥ ውኃ እና በሕዝብ ጤና አጠባበቅ ላይ የሚያተኩሩትን ፕሮጄክቶች(WASH PROJECT) ይፋ ያደረጉት፣ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፣ አገራቸው በቀጣይነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋራ በምታደርገው ትብብር፣ ለ“ዋሽ ፕሮጄክት” ቅድሚያ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል፡፡

እኒኽን መሰል ፕሮጄክቶች፣ ኢትዮጵያ የንጹሕ መጠጥ ውኃን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ የያዘችውን የ10 ዓመት ዕቅድ ለማሳካት እንደሚያግዛት፣ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG