በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩኤስኤአይዲ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳይሬክተር ወደ ጋምቤላ አቀኑ


የዩናይትድ ስቴትሱ ዓለም አቀፍ ልማት እና ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ድሬክተር ስካት ሆክላንደር፣ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ
የዩናይትድ ስቴትሱ ዓለም አቀፍ ልማት እና ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ድሬክተር ስካት ሆክላንደር፣ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

የዩናይትድ ስቴትሱ ዓለም አቀፍ ልማት እና ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ተልዕኮ ድሬክተር ስካት ሆክላንደር ወደ ጋምቤላ የተጓዙት፡ በክልሉ ያለውን የስደተኞች የእርዳታ ምግብ ዕደላ አጀማመር እና ድርጅታቸው የወባ ወረርሽኝን ለመዋጋት በአካባቢው የሚያካሂዳቸውን ፕሮጀክቶች ይዞታ ለማየት መሆኑን ድርጅቱ ያወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የንጉኒኤል እና ፑግኒዶ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎችን የጎበኙት የዩኤስኤአይዲ ድሬክተር የድርጅታቸው አጋር በሆነው ወርልድ ቪዥን የተዘጋጀውን የህይወት አድን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ዕደላ ተዘዋውረው መመልከታቸውን ዘገባው ጠቁሟል።

ዳይሬክተሩ በተጨማሪም፡ የጣት አሻራዎ አጠቃቀምን እና የምግብ ከረጢቶች ላይ የሚቀመጡ ዲጂታል መለያዎችን ጨምሮ፡ የምግብ እርዳታው ለተረጂዎች በትክክል መድረሱን ለማረጋገጥ የሚረዱ፡ በስደተኞች የምግብ ዕርዳታ ስርጭት ዙሪያ በቅርቡ የተተገበሩ ማሻሻያዎችን ተመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG