በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳማንታ ፓወር የኢትዮጵያ ጉዞ


ፎቶ ፋይል፦ የዩኤስኤድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር
ፎቶ ፋይል፦ የዩኤስኤድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር

በነገው ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሚጠበቁት የዩኤስኤድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር፣ በትግራይ ክልል ረሃብን ለመከላከል የተሟላ እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት እንዲፈቀድ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ግፊት ማድረግ የጉዟቸው ዓላማ እንደሆነ አስቀድመው ገልጸዋል፡፡ ይሁን እና የሚያደርጉት ግፊት ስለሚያካትታቸው ነጥቦች የተባለ ነገር የለም፡፡

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግን በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ስለ ሳማንታ ፓወር ጉብኝት ባይገልጹም፣ በሱዳን በኩል የሰብዓዊ ድጋፍ መተላለፊያ መስመር እንዲከፈት የሚደረግ ያሉትን ጫና በጽኑ ተቃውመዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጫናውን “ግልጽ የሆነ የተንኮል ወጥመድ” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል በማለት የሚጠራው ኃይል መሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ጄነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች በኩል ጥቃት የከፈቱት፣ ትግራይ የተዘጉባትን በሮች ለመክፈት እና የትግራይ መንግሥት ብለው በገለጹት አካል የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲቀበል ጫና ለማሳደር መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሳማንታ ፓወር የኢትዮጵያ ጉዞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:52 0:00


XS
SM
MD
LG