በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳማንታ ፓወር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር

የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር በሚቀጥለው ሳምንት ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ።

የጉብኝታቸው ዓላማ በግጭት በተጎዳው እና የከባድ ረሃብ ስጋት እየጨመረ ወደ አለበት የትግራይ ክልል የሰብዓዊ ረድኤት ተደራሽነት እንዲኖር ግፊት ለማድረግ መሆኑን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

ዩኤስኤድ ባወጣው መግለጫ ሳማንታ ፓወር በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናትን በማነጋገር በትግራይ ክልል ረሃብን ለመከላከል ያልተገደበ የሰብዓዊ ረድኤት ተደራሽነት እንዲፈቀድ እና በሌሎችም በግጭት በተጎዱ የኢትዮጵያ አካባቢዎች አጣዳፊ ችግር ላይ ላሉ ሰዎች መድረስ የሚቻልበት መንገድ እንዲመቻች ግፊት እንደሚያደርጉ አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ዋና አስተዳዳሪ ፓወር ነገ ቅዳሜ በሚጀምረው ጉዟቸው ሱዳንንም እንደሚጎበኙ መግለጫው አስታውቆ፣ በዚያ ከበርካታ አሰርት አምባገነን አገዛዝ በኋላ የተቋቋመውን በሲቪሎች የተደገፈ የሽግግር መንግሥት ለማገዝ ምዕራባዊያን ሃያላን ጥረት እያደረጉ መሆኑን ዘገባው አክሏል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደትግራይ ተጨማሪ እርዳታ የማይደርስ ከሆነ መቀሌ ከተማ ከዚሁ የአውሮፓ ሃምሌ ወር በኋላ ችግር ላይ ላሉ ሰዎች የሚታደል ምግብ እንደማይኖር አስጠንቅቋል።

በቅርቡ የምግብ እርዳታ በጫኑ የዓለም የምግብ ፕሮግራም የጭነት መኪናዎች ኮንቮይ ላይ ከደረሰው ጥቃት ወዲህ ወደትግራይ የሚያስገቡ መንገዶች በሙሉ በጸጥታ ችግር የተዘጉ መሆናቸውን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG