በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምግብ ቀውስ ማቃለያ ድጋፍ ሰጠች


ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዲስ አበባ
ዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አዲስ አበባ

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምግብ ደኅንነት ድጋፍ የሚውል ወደ 55 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ መስጠቷን ኤምባሲዋ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

እርዳታው የተሰጠው በዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) አማካይነት መሆኑን ኤምባሲው አመልክቷል፡፡

ኢትዮጵያ “በሩሲያው የዩክሬን ወረራ ምክንያት የተፈጠረ ከፍተኛ የምግብና የዋጋ ውድነት እያስተናገደች መሆኗን” ያመለከተው ይህ መግለጫ ዩኤስኤአይዲ ይህንን አዲስ ድጋፍ የለቀቀው ከዚህ ጋር ተያይዞ ወደፊት የሚፈጠረውን ተጨማሪ የምግብ ቀውስ ለመቋቋም የሚያስችል ምላሽ ለመስጠት መሆኑን ኤምባሲው አክሎ አስታውቋል።

ለኢትዮጵያ ህዝብ የተሰጠው ይህ ድጋፍ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እኤአ ባላፈው ሰኔ ጀርመን ውስጥ በተካሄደው በቡድን 7 አገሮች መሪዎች ጉባዔ ላይ በተባባሰው ዓለምአቀፍ የምግብ ቀውስ እጅግ የተጎዱ አገሮችን ለመርዳት ዩናይትድ ስቴትስ የ2.7ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንድምትሰጥ ባስታወቁት መሠረት መሆኑን የኢምባሲው መግለጫው አስታውሷል።

ዩኤስኤአይዲ ይህን አዲስ የገንዘብ ድጋፍ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የውኃና የአቅርቦት ሥርዓት የወደመባቸውን ጨምሮ በዩክሬን ጦርነት ቀውስ ኢትዮጵያ ውስጥ በጣም የተጎዱ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት የሚጠቀምበት መሆኑን ኤምባሲው አስረድቷል።

የኢትጵያን የምግብ ምርት አቅም ለማሳደግ ከ3ሺ500 በላይ የሆኑ የእርሻ ንግዶችን፣ በእጅጉ የተጎዱ አርብቶ አደሮችና ማኅበረሰቦችንም ዩኤስኤአይዲ እንደሚረዳ መግለጫው አክሎ ገልጿል።

XS
SM
MD
LG