በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳማንታ ፓወር ከሰላም ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር

ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖር እና ግጭት መቆም እንዳለበት ከሰላም ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤድ) ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ገለጹ።

ከውይይታቸው በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት የድርጅቱ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ለግጭቱ ወታደራዊ አማራጭ መፍትሔ እንደማይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ አለበት ብለዋል፡፡

"ግጭቱን ለመፍታት ውይይት መጀመር አለበት” ያሉት ፓወር የተለያዩ ኃይሎች፣ ማለትም የህወሓት፣ የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎች ከያዟቸው የራሳቸው ያልሆኑ ካሏቸው ስፍራዎች መውጣት እንዳለባቸውም ተናግረዋል። በአፋር እና በአማራ ክልሎች በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ስለመፈናቀላቸው መረዳታቸውንም ተናግረዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲውል በቅርቡ ይፋ ያደረገችውን 149ሚሊዮን ዶላር የጠቀሱት ፓወር፣ ለኢትዮጵያ የጤና እና የሰብዓዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውል ተጨማሪ 45ሚሊዮን ዶላር መጽደቁንም በዛሬው መግለጫቸው ይፋ አድርገዋል፡፡

በሌላ በኩል ከሳማንታ ፓወር ጋር በተደረገው ውይይት ተጨማሪ የሰብዓዊ አገልግሎት መስመር እንዲከፈት የሚል ጥያቄ እንዳልተነሳ የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ገልፀዋል።

የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ምሽት ላይ ከ(ዩ ኤስ ኤድ) አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ጋር ከተወያዩ በኋላ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

መንግሥት የሰብዓዊ አገልግሎት በትግራይ ክልል ተደራሽ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ እና በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለመረዳት ፓወር ወደ ኢትዮጵያ በመምጣታቸው ደስተኛ መሆኑንም ነው ወ/ሮ ሙፈሪያት ተናግረዋል፡፡ እርዳታ በአግባቡ እንዲደርስ ካስፈለገ ህወሓት ከፀብ አጫሪ ድርጊቱ እንዲቆጠብ ጫና ሊደረግበት እንደሚገባ መንግሥት በውይይቱ ላይ ማሳሰቡን ወ/ሮ ሙፈሪያት ገልጸዋል፡፡

ከመንግሥት የተናጥል ተኩስ አቁም ውሳኔ በኋላ ህወሓት በከፈተው ጥቃት ምክንያት በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች ስለመፈናቀላቸውም ያነሱት ሚኒስትሯ፣ የሰብዓዊ አገልግሎት ድርጅቶች ከትግራይ ክልል በተጨማሪ እነዚህን ተፈናቃዮችም ሊደርሱ እንደሚገባ በውይይታቸው መነሳቱንም ጠቁመዋል፡፡

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

ሳማንታ ፓወር ከሰላም ሚኒስቴር ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:31 0:00


XS
SM
MD
LG