በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካውያን ፓርቲ ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል


የዩናይትድ ስቴትስ ሪፖብሊካውያን ፓርቲ ጉባኤ፣ ዛሬ ማታ ይጀመራል። ፕሬዚዳንድት ዶናልድ ትረምፕ ድርጅታቸን ወክለው እንደገና ለፕሬዚዳንትነት እንዲወዳደሩ ይሰየማሉ።

ለአራት ምሽቶች በሚዘለቀው የሪፖብሊካውያን ፓርቲ ጉባኤ፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕ በዲሞክራቱ ተወዳዳሪያቸው ጆ ባይደን ላይ፣ የቃላት ጥቃት ውርጅቢኝ ያደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ዲሞክራቶች ባለፈው ሳምንት በኮሮናቫይረስ ስጋት ምክንያት፣ በቨርቹዋል ወይም በርቀት ባካሄዱት ጉባኤ፣ ጆ ባይደን ዲሞክራስያዊ ፓርቲውን ወክለው ለፕሬዚዳንትነት እንዲወዳደሩ መሰየማቸው የሚታውስ ነው።

ሪፖብሊካውያኑ ግን ዛሬ ማታ፣ በሻርለት ሰሜን ካሮላይና በአካል ተገናኝተው ፕሬዚዳንት ትረምፕን፣ ድርጅቱን ወክለው እንደገና እንዲወደረሩ ይሰይማሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከማክሰኞ እስከ ሀሙስ ባለው ጊዜ ግን፣ አብዛኛው እንቅስቃሴ ዋሽንግተን ይሆናል ተብሏል።

XS
SM
MD
LG