በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴሞክራቲክ ፓርቲው የማክሰኞ ማምሻ


የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን ትናንት ምሽት በዴክሞክራቲክ ፓርቲው ጉባዔ ላይ ፕሬዚዳንት ኦባማን ዳግም ለማስመረጥ ታሪካዊና ቀስቃሽ ንግግር አድርገዋል፡፡

ቢል ክሊንተን በዚሁ ንግግራቸው “የምትፈልጉት አሸናፊ ሁሉንም ይወስዳል፤ የአንተ ሕይወት ግን የራስህ ጉዳይ ነው የሚባልበትን ሕብረተሰብ ከሆነ መምረጥ ያለባችሁ የሪፐብሊካኑን ዕጩዎች ነው፡፡ የምትፈልጉት ግን ዕድሎቹን የሚጋራ፣ ኃላፊነቶቹንም የሚጋራ ኅብረተሰብን ከሆነ ድምፃችሁን መስጠት ያለባችሁ ለባራክ ኦባማና ለጆ ባይደን ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ክሊንተን አክለውም የሪፐብሊካኑ የመጀመሪያ ቅድሚያ “አሜሪካን መልሶ ወደሥራ ማስገባት ሳይሆን ፕሬዚዳንቱን ከሥራ ውጭ ማድረግ ነበረ” ብለዋል፡፡

የተወልደ ወልደገብርዔልን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG