በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ አሸባሪዎችን በተመለከተ ሥምምነት ተፈራረሙ


ዩናይትድ ስቴትስና ኢትዮጵያ በቅርቡ አሸባሪዎችን ለይቶ የማጣራት መረጃን የመለዋወጥ ሥምምንት መፈረማቸውን አዲስ አባበ ያለው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ጠቁሟል።

በዩናይትድ ስቴትስ በኩል ሥምምነቱን የፈረሙት፣ የፌደራል ምርመራ ቢሮ ረዳት ሥራ አስኪያጅና የዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪዎችን አጣርቶ የመለየት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ ቻርልስ ኤች ኬብል ሲሆኑ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የሀገሪቱ ብሄራዊ የሥለላና የደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ገብረሚካኤል ናቸው።

ሥምምነቱ ሁለቱ ሀገሮች የአሸባሩነትን ተግባር ለመከላከል ያላቸውን ብቃት ለማጠናከር ሲሉ መረጃ ለመለዋወጥ የሚችሉበትን አሰራር ይቀይሳሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG