በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛምቢያ የነበሩትን አምባሳደሩን መለሰ


አምባሳደር ዳንዬል ፉትን
አምባሳደር ዳንዬል ፉትን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛምቢያ የነበሩትን አምባሳደሩን መለሰ።

ዳንዬል ፉትን ከአምባሳደርነታቸው እንዲነሱ የወሰነው ዛምቢያ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የፈፀሙ ፍቅረኞችን ማሰሯን አጥብቀው ከተቹ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

የዛምቢያ ፕሬዚዳንት ኤድጋር ሉንጉ ከአሁን ወዲይ ከኚህ አምባሳደር ጋር መስራት አልፈልግም በማለታቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአምሳደሩ ከእንግዲህ እዚያ መቆየት ምክንያታዊ አይሆንም ከሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን አመልክቷል።

ዛምቢያ በዩናያትድ ስቴትስ አምባሳደሩ መመለስ ጉዳይ እስካሁን አስተያየት አልሰጠችም። ዛምቢያ በየዓመቱ ከዩናያትድ ስቴትስ የብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር ዕርዳታ ታገኛለች፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG