ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት በቀረበለት የወሲብ ብዘበዛና ጥቃት ሳቢያ 450 የሚደርሱ የጋቦን ሰላም አሰካባሪዎችን ከማዕከላዊ አፍሪካ እያስወጣ መሆኑን የጋቦን መንግሥት አስታወቀ፡፡
የጋቦን መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት ረቡዕ በሰጠው መግለጫ ጉዳዩን መመርም መጀመሩን ገልጾ፣ በምርመራው የሚገኝ ነገር ካለ በወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ የሚታይ ይሆናል ብሏል፡፡
የመንግሥታቱ ድርጅት እኤአ ከ2013 ጀምሮ በማዕከላዊ አፍሪካ የሚካሄደውን በሃይማኖቶችና በማህበረሰቦች መካከል የሚካሄደውን የርስ በርስ ግጭት ለማብረድ፣ ጋቦን ውስጥ እስካሁን ወደ አስርሺ የሚጠጉ የሰላም አሰካባሪ ኃይሎችና ሠራተኞች እንዳሉትን ተመልከቷል፡፡