በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስኖውደን የሩሲያን ፓስፖርት ተቀበለ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ኮንትራክተር ሠራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ኮንትራክተር ሠራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን

የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የመረጃ ተቋም (NSA) በሚስጢር የሚያደርጋቸውን በርካታ የስለላ መረቦችን ያጋለጠው የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ የደህንነት ኮንትራክተር ሠራተኛ ኤድዋርድ ስኖውደን ለሩሲያ ያለውን ታማኝነት በመግለጽ የሩሲያን ፓስፖርት መቀበሉን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

የስኖውደን ጠበቃ አናቶሊ ኩቼሬና “አዎ ፓስፖርቱን አግኝቷል ቃለ መሃላውንም ፈጽሟል” ብለው ለሩሲያ መንግሥት የዜና ወኪል ታስ መናገራቸውም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

የ39 ዓመቱ ስንውደን ስለ ዘገባው አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠየቅም ምላሽ አለመስጠቱን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቫላድሚር ፑቲን ባላፈው መስከረም ዩናይትድ ስቴትስና አጋሮችዋ ሰዎችን በድብቅ ይቀዳሉ የተባሉበትን የሚስጥር ሰነዶች በማጋለጥ ለኮበለለው ስኖውደን የሩሲያን ዜግነት መስጠታቸው ተነግሯል፡፡

የስኖውደን ደጋፊዎች የዩናይትድ ስቴትስን የስለላ መጠን ያጋለጠ የዘመናችን ሰው በማለት ሲያወድሱት ተቃዋሚዎቹ ደግሞ የምዕራባውያን ሰላዮች የሚጠቀሙባቸውን ዘዴዎች ለጠላት አገሮችና ለታጣቂ አማጽያን አሳልፎ በመስጠት የሰዎችን ህይወት ለአደጋ አሳልፎ የሰጠ ከሃዲ ነው ሲሉ ይከሱታል፡፡

XS
SM
MD
LG