በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ በኢትዮጵያና ኤርትራ ጉዳይ


ኢትዮጵያና ኤርትራ ለረጅም ጊዜ የቆዩትን ልዩነቶቻቸው ለመፍታት በቅርቡ እየወሰዱ ያሉት ዕርምጃ አበረታቶናል ስትል ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለረጅም ጊዜ የቆዩትን ልዩነቶቻቸው ለመፍታት በቅርቡ እየወሰዱ ያሉት ዕርምጃ አበረታቶናል ስትል ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አጨቃጫቂዋን ባድመ ከተማን ለኤርትራ መመለስን የሚያካትተውን የአልጀርሱን የሰላም ሥምምነት መሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

ያን ተከትሎ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከትናንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር የኢትዮጵያ የሰላም ሃሳብ የአዎንታዊ አካሄድ ፍንጭ የሚሰጥ ነው በማለት ምላሽ መስጠታቸው መፍትሄ ሊገኝ ነው የሚል ተስፋ ፈንጥቁዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚዳንት በንግግራቸው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን አቋም ለመረዳት እና ስለወደፊት ዕርምጃዎችም ዕቅድ ለመተለም የመንግሥታቸውን ልዑካን ወደአዲስ አበባ እንደሚልኩ አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ሃሙስ ባወጣው መግለጫ “ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እና ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደሰላም የሚያመሩ ዕርምጃዎችን መውሰዳቸው ደፋር አመራር ያሳዩበት ነው” ብሉዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ አያይዞም ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ሃገሮች ግንኙነት ሙሉ በሙሉ እንዲታደስ እና ከሁለቱም ሃገሮች ጋር የምንጋራው የሰላምና የዕድገት ምኞት ዕውን እንዲሆን በጉጉት ትጠብቃለች ብልዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG