በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ጆሴፍ ካቢላ ላለመወዳደር መወሰናቸውን ተቀበለች


የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ
የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ እንደገና ለመመረጥ ላለመወዳደር መወሰናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ በደስታ ተቀብላለች፡፡

የዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፖብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ እንደገና ለመመረጥ ላለመወዳደር መወሰናቸውን ዩናይትድ ስቴትስ በደስታ ተቀብላለች፡፡

ገዢው ፓርቲ አለች ዩናይትድ ስቴትስ የኮንጎ ገዢ ፓርቲ ካቢላን ሳይሆን ሌላ ሰው በዕጩነት ለማቅረብ መወሰኑ የሃገሪቱን ዲሞክራሲ ወደፊት የሚያራምድ ትልቅ ውሳኔ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሂዘር ኖወርት ባወጡት መግለጫ ሚስተር ካቢላ የኮንጎን ህገ መንግሥት እና እኤአ በ2016 የተደረሰውን ሥምምነት ለማክበር ዝግጁ መሆናቸውን የሚያሳይ ርምጃ በመሆኑ አበረታች ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡

አክለውም የኮንጎ ሕዝብ ጥቃት ይደርስብናል ብሎ ሳይሸማቀቅ ሃሳቡን በነፃነት መግለጽ አለበት ብለዋል። የኮንጎ የምርጫ ኮሚሽን እና ባለሥልጣናቱ በመጪው ታኅሳስ ሃያ ሦስት የሚካሄደው ምርጫ ተዓማኒ እንዲሆን አስፈላጊውን ዕርምጃ ሁሉ እንዲወስዱ እናሳስባለን ብለዋል።

ጆሴፍ ካቢላ የቀድሞ የሀገር ግዛት ሚኒስትር ኢማኑኤል ራማዛኒ ሻዳሪ እንዲወዳደሩ ድጋፍ እሰጣለሁ ሲሉ አስታውቀዋል።

ሰማኒያ ሚሊዮን ህዝብ ያላት ያቺ ሃገር ከእውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ነጻ ከወጣችበት እኤአ ከ1960 ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ኖሯት አታውቅም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG