በአሜሪካ የሚታየው አደገኛ የአየር ሁኔታ የቀጠለ ሲኾን፣ በኬንተኪ በተከሰተው ጎርፍ የሞቱትን ስምንት ሰዎች ጨምሮ በድምሩ ዘጠኝ ሰዎች ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ በግዛቲቱ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አውጀዋል። በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከአደጋ መታደግ መቻላቸውን አገረ ገዢው አንዲ በሺር አስታውቀዋል።
አንድ እናትና የሰባት ዓመታ አዳጊ በጎርፍ ውስጥ ከነበረው መኪናቸው ማውጣት እንደተቻለም ታውቋል። አብዛኛው የአሜሪካ ክፍል በቅዝቃዜ የተዋጠ ሲሆን፣ ነፋስ እና በረዶውም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
በጆርጂያ ግዛት አንድ ሰው እንደሞተ ታውቋል።
የአስቸኳይ ጊዜ በታወጀባት ቴነሲ ግድብ ተደርምሶ 300 የሚሆኑ ሰዎች የሚኖሩበት መንደር ተጥለቅልቋል። ከጎርፉ በተጨማሪ መብራት በመቋረጡና ቅዝቃዜው በማየሉ ነዋሪዎች የግድ ከመንደሩ መውጣት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል።
መድረክ / ፎረም