በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ቀዝቅዛለች


ሠራተኛው በረዶን በመጥረግ ሥራ ላይ ይገኛል፤ ሃይማርክ ስታዲየም፣ በኦርቻርድ ፓርክ፣ ኒው ዮርክ እአአ ጥር 14/2024
ሠራተኛው በረዶን በመጥረግ ሥራ ላይ ይገኛል፤ ሃይማርክ ስታዲየም፣ በኦርቻርድ ፓርክ፣ ኒው ዮርክ እአአ ጥር 14/2024

አደገኛ ነው የተባለ ቀዝቃዛ አየር እና በረዶ አብዛኛውን የአሜሪካ ክፍል ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንደሚያዳርስ ሲጠበቅ፣ በየግዛቱ እስከዛሬ ታይቶ የማይታወቅ የቅዝቃዜ መጠን ይመዘገባል ተብሎ ይጠበቃል።

79 በመቶ የሚሆነው የአሜሪካ ክፍል ከዜሮ ዲግሪ ሴልሲየስ በታች የሆነ የቅዝቃዜ መጠን እንደሚያስመዘግብ በመነገር ላይ ነው።

ብሔራዊ የአየር ትንበያ አገልግሎት እንዳለው፣ ከበድ ያለው ነፋስ ሲታከልበት ደግሞ፣ በአንዳንድ ቦታዎች የቅዝቃዜው መጠን ከዜሮ በታች 34 ዲግሪ ሴልሲየስ ሊደርስ ይችላል።

ቅዝቃዜው በረራዎችን ጨምሮ ሌሎችንም የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ሲያስተጓጉል፣ ዛሬ ሰኞ ምሽት በአዮዋ የሚደረገውን “አዮዋ ኮከስ” ተብሎ በሚጠራውንና ግዛቲቱ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩ የምትመርጥበትን ሂደት እንዳያስተጓጉል ተሰግቷል።

ቤት መቀመጥ የለም፣ ቢያማችሁም ወጥታችሁ ድምፅ ስጡ”

“ቤት መቀመጥ የለም፣ ቢያማችሁም ወጥታችሁ ድምፅ ስጡ” ሲሉ ተደምጠዋል፣ ከሪፐብሊካን እጩዎች ከፊት ረድፍ የሚገኙት የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ፡፡

በጥሎ ማለፍ ደረጃ ላይ የሚገኘው እና ተወዳጅ የሆነው የአሜሪካ እግር ኳስ ጨዋታም የቅዝቃዜው ሰለባ ሆኗል። ትናንት ሊደረግ ታቅዶ የነበረው የፒትስበርግ ስቲለርስ እና በፈሎ ቢልስ ጨዋታ፣ ኒው ዮርክ ውስጥ በነበረው ከፍተኛ ቅዝቃዜ ምክንያት ወደ ዛሬ የተሸጋገረ ሲሆን፣ በሌሎች ቦታዎች በተካሄዱት ግጥሚያዎች ደግሞ አንዳንድ ተጨዋቾች ኳሷን ለመቅለብ ሲቸገሩ ተስተውሏል።

“አርክቲክ ስቶርም” ተብሎ በሚጠራው የአየር ክስተት በተፈጠረው ቅዝቃዜ ምክንያት፣ እስከ አሁን አራት ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ሲነገር፣ በሰሜን ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ካለ ኤሌክትሪክ አስቀርቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG