በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ለሽብርተኞች ከለላ ትሰጣለች" በሚል የተከሰሰችው ፓኪስታን

“ለሽብርተኞች ከለላ ትሰጣለች” ተብላ በፕሬዚደንት ትረምፕ የተከሰሰችው ፓኪስታን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚወሰድባትን እርምጃ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀች መሆኗ ተሰማ።

“ለሽብርተኞች ከለላ ትሰጣለች” ተብላ በፕሬዚደንት ትረምፕ የተከሰሰችው ፓኪስታን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የሚወሰድባትን እርምጃ በተጠንቀቅ እየተጠባበቀች መሆኗ ተሰማ።

በዚህም ክስ የተነሳ ፓኪስታን ሀገሯ ላይ ለሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ዴቪድ ሃሊ ተቃውሞዋን እንዳሰማች ይታወቃል።

የአሜሪካ ኃይሎች አፍጋኒስታን ውስጥ እየተዋጓቸው ያሉትን አሸባሪዎች ፓኪስታን ከለላ እየሰጠለች መሆኗን በመጥቀስ ነበር፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ፓኪስታንን የወነጀሉት።

ባለፈው ሰኞ በቀረበው በዚሁ ክስ ፕሬዚደንት ትረምፕ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሞኝነት ባለፉት አሥራ አምስት ዓመታት ለፓኪስታን ከ$33 ቢሊዮን በላይ መስጠቷን አስታወሰው፣ በምትኩ ለእኛ ግን ከውሸትና ከማታለል ሌላ የሰጡን ነገር የለም ነበር ያሉት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG