በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሞስኮ የጦር ወንጀሎችን እየፈጸመች ነው አለች


የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያደረሰች ያለው ጥቃት በቀጠለበት በዲኒፕሮ፣ ዩክሬን በአየር ድብደባ ጥቃቱ ከተጎዱ ሕንፃዎች መካከል እርዳታ እየሰጡ እአአ መጋቢት 11/2022
የአደጋ ግዜ ሰራተኞች ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያደረሰች ያለው ጥቃት በቀጠለበት በዲኒፕሮ፣ ዩክሬን በአየር ድብደባ ጥቃቱ ከተጎዱ ሕንፃዎች መካከል እርዳታ እየሰጡ እአአ መጋቢት 11/2022

ዩናይትድ ስቴትስ ሞስኮ በዩክሬን ላይ የጦር ወንጀሎችን እየፈጸመች ነው ስትል አስጠነቀቀች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ሩሲያ የሚደረገው ድርድር ፍሬ አልባ ሲሆንባት “ሕዝብ በበዛባቸው አካባቢዎች ላይ ጉዳት የማድረስ ስልት ጀምራለች” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ምንም እንኳን ሩሲያ የጦር ወንጀሎችን ፈጽማለች ብለው ለይተው ባይከሱም “በጄኔቫ ኮንቬንሽን የሰብዓዊ የጦር ወንጀሎች ተብለው የተቀመጡትን ዓይነት ሲቪሎችን ሆነ ብሎ የማጥቃት አካሄዶች መኖራቸውን ከታመኑ ሪፖርቶች አይተናል” ብለዋል፡፡

ኔድ ፕራስ “ፑቲን በፍጥነት ዩክሬንን የሚቆጣጠር መስሎት ነበር ነገር ግን እንዳልተሳካለት ግልጽ ነው” ያሉ ሲሆን “አሁን ደግሞ ፊቱን በሲቪል ዜጎች ላይ አደጋ ወደ ማድረስ አዙሮ የዩክሬንን ሕዝብ ቅስም ሊሰብር እየጣረ ነው ነገር ግን የሚሳካለት አይሆንም” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ሩሲያ በዩክሬን ወረራ ሲቪሎችን ዒላማ አድርጋለች መባሉን አልተቀበለችውም፡፡

XS
SM
MD
LG