በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራቶች በየግዛቶቹ የወጡትን የመራጮች መብት ገደብ እየታገሉ ነው


አትላንታ ጆርጂያ ውስጥ የመምረጥ መብትን ለመገደብ ወጥቷል ያሉትን ህግ የተቃወሙ አሜሪካውያን በጆርጅያ ምክር ቤት ፊት ለፊት፣ እኤአ ማርች 8 2021
አትላንታ ጆርጂያ ውስጥ የመምረጥ መብትን ለመገደብ ወጥቷል ያሉትን ህግ የተቃወሙ አሜሪካውያን በጆርጅያ ምክር ቤት ፊት ለፊት፣ እኤአ ማርች 8 2021

በደቡብ ዩናይትድ ስቴትስ ጆርጅያ ክፍለ ግዛት በፖስታ ቤት በኩል የሚላከውን የድምጽ አሰጣጥ ለመገደብ፣ የመራጮችን ማንንነት አጥብቆ ለማጣራት የወጣው አዲሱ ህግና፣ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የመምረጥ መብት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ክርክር አስነስቷል፡፡

የዴሞክራቲክ ፓርቲ ሕግ አውጭዎች ምንም እንኳ በአሜሪካው የህግ መወሰኛ ምክር ቤት የማለፍ እድሉ አነስተኛ ቢሆንም፣ በመምረጥ መብት ህጎች ዙሪያ ያሏቸውን አማራጮች እየተመለከቱ ነው፡፡

ከ2020ው ምርጫ ማግስት በኋላ፣ በመላው አገሪቱ፣ ምርጫውን በሚመለከት አዲስ ስጋት ተከስቷል፡፡

በየቦታው ያሉት ዜጎችና፣ አንዳንድ የቢዝነስ ተቋማት ሳይቀሩ፣ ፕሬዚዳንት ባይደን በጠባብ ልዩነት ባሸነፉበት የጆርጅያ ክፍለ ግዛት፣ የወጣው አዲሱ ህግ፣ “አነሰተኛ ቁጥር ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎችን ያገለለ ነው” በማለት ይቃወሙታል፡፡

የዴሞክራቱ ህግ አውጭ ሴንተር ዲክ ደርባን እንዲህ ይላሉ

“በጆርጅያ ያሉት ሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች በምርጫው ላይ ያላቸውን ችግር የድምጽ አሰጣጡን በማክበድ ሊወጡት የወሰኑ ይመስላል፡፡ ምክንያቱም ባላፉት ምርጫ ድምጽ የሰጡት መራጮች የእነሱ መራጮች አይደሉም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከመሰረቱ አሜሪካዊ አይደለም፡፡”

ዲሞክራቶች እንደሚሉት፣ ባለፈው ዓመት ውስጥ ብቻ፣ የመምረጥ መብትን የሚያከብዱ 360 ህጎች 47 ክፍለ ግዛቶች ውስጥ ወጥተዋል፡፡

ሪፐብሊካኖች ደግሞ፣ ዴሞክራቶች የምርጫውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰዱ ርምጃዎችን በሙሉ እየተቃወሙ ነው ሲሉ ይከሷቸዋል፡፡

ሪፐብሊካኑ ሴንተር ቸክ ግራስሊ እንዲህ ብለዋል

“ይህ በጣም ቀላል ነው፡፡ የምርጫውን ተአማኒነት ለማስከበር ህግ ባወጡ ክፍለ ግዛቶቻችን ላይ የተቃጣ የቅርብ ጊዜው ጥቃት ነው፡፡ አገር አቀፍ ዴሞክራቶችና ትላልቅ የቢዝነስ ተቋማት በወጣው የድምጽ አሰጣጥ ህግ የተነሳ ጆርጅያን ለማስፈራራት ወስነዋል፡፡”

ዴሞክራቶች በየግዛቶቹ የወጡትን የመራጮች መብት ገደብ እየታገሉ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:07 0:00

በ2020ው ምርጫ አነስተኛ ቁጥር ያላቸውን የማህበረሰብ አባላት በነቂስ እንዲወጡ አድርገዋል የሚባሉት እንደ ስቴሲ አብርሃም ያሉት አክቲቪስቶች ደግሞ “አዲሶቹ ህጎች አዳዲሶቹ የዘር መድልዎ መልኮች ናቸው” ይላሉ፡፡ እንዲህ ይላሉ ስቴሲ

“በርግጥ የዘረኝነት ይዘት ያሉበትም ክፍሎች አሉት፡፡ ምክንያቱም የተወሰኑ የማህበረሰብ ክፍል መራጮችን ባርህይ በመጥቀስ፣ በምርጫው እንዳይሳተፉ ለመገደብ ወይም ጨርሶ ለማጥፋት የተጠቀሙበት የዘር ማጥላላትም አለ፡፡”

ዴሞክራቶቹ በሚቆጣጠሩበት የተወካዮች ምክር ቤት የወጡ የመምረት መብት ህጎች፣ የምርጫውን ደንቦች አገር አቀፍ ደረጃ ያላቸው እንዲሆኑ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

ሪፐብሊካኖች ግን፣ ይህ የክፍለ ግዛቶችን ሥልጣን የሚነጥቅ ነው በማለት ይቃወሙታል፡፡

ዲሞክራቶች እጅግ በጠበበ መንገድ አብላጫውን በተቆጣጠሩበት የህግ መወሰኛው ምክር ቤት የዴሞክራቶቹ ህግ የማለፍ እድሉ በጣም አነስተኛ መሆኑም ተመልከቷል፡፡

(የቪኦኤ የምክር ቤቶች ዘጋቢ፣ ካትሪን ጊፕሰን፣ ከላከቸው ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG