በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሥልጣን ርክክቡን ሂደት ትረምፕና ሪፐብሊካኖች እያጣጣሉት ነው


ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ የትረምፕ አስተዳደር፣ ሰላማዊውን የሥልጣን ሽግግር ለመጀመር አለመፈለጉንና ቁልፍ የሆኑ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ፣ የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት ለመቀልበስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በህግ ለመፋለም መነሳታቸውን አልተቀበሉትም፡፡ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳኩስዋራ ዘገባ ይዘናል፡፡

የዓለም መንግሥታት፣ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦርስ ጆንሰንና የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማርኮን ጨምሮ፣ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት፣ ጆ ባይደን፣ የደስታ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ አገር ውስጥ ያለው ሁኔታ ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፓምፔዮ እንዲህ ይላሉ፡፡

“ወደ ሚቀጥለው የፕሬዚዳንት ትረምፕ ሁለተኛው አስተዳደር ምንም ችግር የሌለበት ሽግግር ይካሄዳል”

የአገሪቱ ዋና ዲፕሎማት፣ ማይክ ፓምፔዮ፣ የምርጫውን ውጤት አልተቀበሉትም፡፡ የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕን፣ ህጋዊ የሆኑትን ድምጾች ብቻ እንጂ ህገወጦቹን ድምጾች አትቁጠሩ፣ የሚለውንና“ዴሞክራቶች ምርጫውን ሰርቀውታል” የሚለውን መሠረት የሌለውን ክስ መልሰው ደግመውታል፡፡

ጆ ባይደን ስለዚህ እንደዚህ ይላሉ

"ፕሬዚዳንቱም ሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓሞፔዮ እህም ፓምፔዮ … የተናገሩት ነገር ምንም መሰረት የለውም" ብለዋል።

በትናንትናው እለት፣ ጆ ባይደን ሲናገሩ፣ ትረምፕ ምርጫውን አልቀበልም ማለታቸው የሚያሳፍር መሆኑንበመግለጽ አጣጥለውታል፡፡

“ምርጫውን ያሸነፍን መሆኑን መቀበል አለመፈለጋቸው፣ ከዚህ ወቅት አንስቶ እስከ ጥር 20 ድረስ፣ በምናደርገውና ልናደርግ ባቀደነው ነገር ሁሉ ላይ የሚያስከትለው ነገር አይኖርም፡፡” ብለዋል፡፡

ጆ ባይደንና አጋራቸውን ከማላ ኻሪስን፣ “እንኳን ደስ ያላችሁ” ያሉት የሪፐብሊካን ሴንተሮች፣ በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ከፓርቲው መካከል፣ የቀድሞ ፕሬዚዳትን ጆርጅ ቡሽ የደስታ መግለጫቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፣ አብዛኞቹ የሪፐብሊካን ፓርቲ መሪዎች ግን፣ ከፕሬዚዳንት ትረምፕ ጋር ተሰልፈዋል፡፡ ለምሳሌ የሴነቱ መሪ ሪፐብሊካኑ፣ ሚች መካኔል እንዲህ ብለዋል

“ፕሬዚዳንት ትረምፕ የምርጫውን ሂደት መዛባት አስመልከቶ ጥያቄ ማንሳትም ሆነ ያላቸውን የህግ አማራጮቻቸውን የማየት መቶ በመቶ መብቱ አላቸው፡፡”

የሪፐብሊካን ስትራጂስት የሆኑት ራብ ስቱትዝማን እንደሚሉት አብዛኞቹ ሪፐብሊካኖች በግላቸው፣ ባይደን የሚቀጥለው ፕሬዚዳንት እንደሚሆኑ ቢያምኑም፣ ፕሬዚዳንት ትረምፕን መቃረን ግን አልፈጉም፡፡ እንደሚከተለው ያብራሩታል

“ይሄ የፖለቲካ ስሌት የሚያሳየው ከዶናልድ ትራምፕ ጋር መስቀለኛ መንገድ ላይ መገናኘት አለመፈለግን ነው፡፡ ያንድ ማድረግ በአንዲት የቲውት መልኧክት ግማሹን ሪፐብሊካን ፓርቲ ግልብጥ ሊያስደርግብህ ይችላል፡፡ ያንን ራስ ምታት ማንም አይፈልገውም፡፡”

የጥር 20ው በዐለ ሲመት የሚከበርበት ዝግጅት ማወቀሩ ግን ተጀምሯል፡፡ ይፋ የሆነው የርክክብ ሂደቱ ግን፣ በትረምፕ አስተዳደር የሚታዘዘው፣ የፌደራል ጠቅላላ አስተዳደር፣ እስከሚያስታውቅበት ጊዜ ይቆያል፡፡

የአስተዳደር ኃላፊዋ ግን፣ እለቱ መች ሊሆን እንድሚችል፣ እስካሁን አልገለጹም፡፡ እየተሸኘ ያለው አስተዳደር፣ የሚያደርግለት ትብብር በሌለበት ሁኔታ ውስጥ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት ያገለገሉት፣ የጆ ባይደን ልምድ ፣ ጠቃሚ ይሆናል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ በቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ ፣ በሚለር ማዕከል፣ የፕሬዚዳንታዊ ጥናቶች ድሬክተር ባርባራ ፔሪ፣ ስለዚሁ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ

“ዋይት ሀውስን ያውቁታል፡፡ ቢሮክራሲውና ሥራ አስፈጻሚው አካል እንዴት እንደሚሰራም ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ የርክክብ ቡድናቸውን ሲያዋቅሩ ዋሽንግተንን እንዴት እንደሚሰራ በሚያውቁና ልምድ ባላቸው ሰዎች ይሆናል፡፡

በትናንትናው እለት፣ የጆ ባይደን ቡድን፣ በእያንዳንዱ የመንግሥት አስተዳደር ኤጀንሲዎች ውስጥ፣ ያሉትን ሁኔታዎች በመቃኘት፣ የሥልጣን ርክክቡና ሽግግሩ፣ በጥሩ ሁኔታ የሚካሄድበትን መንገድ የሚያመቻቹ፣ ግለሰቦችን ስም አስታውቋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የሥልጣን ርክክቡን ሂደት ትረምፕና ሪፐብሊካኖች እያጣጣሉት ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:06 0:00


XS
SM
MD
LG