በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የተፈጸመው የጅምላ ግድያ እንደሚያሳስባት ገለፀች


ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ
ፎቶ ፋይል፦ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ

በድጋሚ የታደሰ፦

በኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሞቱበት የጅምላ ግድያ ዙሪያ ተቃውሞዋን ያሰማችው ዩናይትድ ስቴትስ ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዲቻል እንደ አዲስ ጥሪ አቅርባለች።

ከጥቃቱ የተረፉ ሰዎች ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል እንደተናገሩት የአማራ ተወላጅ የሆኑ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ኦሮምያ ውስጥ ባሉ አማጽያን መገደላቸውንና አስከሬኖችም ከጥቃቱ ሰዓታት በኋላ መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ እንደነበር የዜና ወኪሉ ዘግቧል።

የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ መ/ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ “አሰቃቂው ድርጊት” አሜሪካንን “እጅግ እንዳሳሰባት” ገልፀው “ኢትዮጵያውያን ጥቃትን እንዲያወግዙና ልዩነቶችን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱ ጥሪ እናደርጋለን” ብለዋል።

ቃል አቀባዩ አክለው “ብሔራዊ ዕርቅ ሁሉን አቀፍና፣ የተጠቂዎችም ሆነ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ፈጻሚዎቹ ፍትህ የሚሰጥበት መሆን አለበት” ብለዋል። የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ጥቃቱ የተፈጸመው የኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ድርጅት አድርጎ በፈረጀው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እንደሆነ ተናግሯል።

የሰራዊቱ ቃል አቀባይ ግን ጥቃቱ የተፈጸመው በራሱ በመንግሥት ሚሊሺያዎች መሆኑንና ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG