ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ምክልት ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ፣ በቬትናሙ ጉብኝታቸው፣ አሜሪካ ከቬትናምጋር ያላትን ግንኙነት ከማጠናከር ጋር፣ለሰብአዊ መብትጉዳዮችም ትኩረት እንደምትሰጥከአገሪቱ መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ማሳሳባቸውን አስታውቀዋል፡፡
ከቬትናም መሪዎች ጋር በተለይ የታሰሩ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ስለመፍታት የተነጋገሩ ቢሆንም የተደረሰበትን ውጤት አልገለጹም፡፡
ቬትናም የንግግርና፣ የፕሬስን ነጻነት፣ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች በማዋከብና በሰብ አዊ መብት ጥሰት በዓለም አቀፍ ደረጃ ብርቱ ወቀሳ ይቀርብባታል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቷ በሰሞኑ ጉብኝታቸው ከሲንጋፕሩና ከቬትናም ጋር በተለያዩ በርካታ ጉዳዮች መስማምታቸውን ተናግረዋል፡፡