በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ በጋዛ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጥሪ አቀረቡ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በአላባማ ግዛት በምትገኘው ሰልማ ከተማ እአአ መጋቢት 3/2024
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በአላባማ ግዛት በምትገኘው ሰልማ ከተማ እአአ መጋቢት 3/2024

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ትላንት እሁድ ጥሪ አቀረቡ። የካማላ ጥሪ ጦርነቱን ለማስቆም የባይደን አስተዳደር እስካሁን ካቀረበው ተማጽኖ ጠንከር ያለው መሆኑ ተገልጿል።

ሃሪስ በ1960ዎቹ በአላባማ ግዛት በምትገኘው ሰልማ ከተማ ውስጥ የተካሄደው የሲቪል መብቶች እንቅስቃሴ መታሰቢያ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር "በጋዛ ካለው ከፍተኛ ስቃይ አንጻር አሁኑኑ የተኩስ አቁም ሊደረግ ይገባል" ብለዋል።

የባይደን አስተዳደር ከግብፅ እና ከኳታር ጋራ በመተባበር፣ በሐማስ የተያዙትን ቀሪ እስረኞች ለማስወጣት እና የተባበሩት መንግሥታት የረሃብ አደጋ እያንዣበበ መሆኑን በሚገልፅበት ጋዛ አፋጣኝ ርዳታ ለማስገባት የሚያስችል የስድስት ሳምንት ተኩስ አቁም እንዲደረግ ሲሠራ ቆይቷል።

ከ59 ዓመታት በፊት የግዛቷ ወታደሮች የአሜሪካ ሲቪል መብት ተሟጋቾችን በጥይት በደበደቡበት እና "በደም የታጠበው እሁድ" በመባል በሚጠራው ኤድመንድ ፔተስ ድልድይ ላይ ቆመው ንግግር ያደረጉት ሃሪስ፣ “የጋዛ ነዋሪዎች ረሃብ ላይ ናቸው” ብለዋል።

እየተደረገ ያለው ከሰብአዊነት የወጣ ነው። ሰብአዊነታችን እርምጃ እንድንወስድ ያስገደናል"

"እየተደረገ ያለው ከሰብአዊነት የወጣ ነው። ሰብአዊነታችን እርምጃ እንድንወስድ ያስገደናል" ያሉት ሃሪስ "የእስራኤል መንግሥት የርዳታ ፍሰቱን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የበለጠ መሥራት አለበት። ምንም ዓይነት ሰበብ ሊኖር አይችልም" ሲሉ በአፅንዖት ተናግረዋል።

ቅዳሜ እለት የዩናይትድ ስቴትስ እና የዮርዳኖች አየር ኃይል ኃይሎች ባደረጉት ዘመቻም፣ በጋዛ ባህር ዳርቻ ላይ 38 ሺህ ምግቦች ከአውሮፕላን ላይ ጥለዋል።

ኻሪስ ንግግሩን ያደረጉት ከእስራኤል የጦር ካቢኔ አባል ቤኒ ጋንቴዝ ጋር ዛሬ ሰኞ በዋይት ኃውስ ለመነጋገር ከተያዘው ቀጠሮ ቀደም ብለው ሲሆን፣ የባይደን አስተዳደር መጋቢት አንድ በሚጀመረው የሙስሊሞች ቅዱስ ረመዳን ወር የተኩስ አቁም ይጀመራል ብሎ ተስፋ ያደርጋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG