ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ “ቻይና በአሜሪካ ዲሞክራሲ ላይ ጣልቅ ትገባለች” በማለት ዛሬ ባደረጉት ንግግር ከሰዋል።
“ቻይና በአሜሪካውያን አመለካከት ላይ፣ በያዝነው ዓመት ምርጫና እአአ በ2020 በሚካሄደው ምርጭ ህዋ ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር እየጣረች ነው” ሲሉ ማይክ ፔንስ “ሀድሰን” በተባለው ወግ አጥባቂ ተቋም ባደረጉት ንግግር ገልፀዋል።
ፔንስ አያይዘውም በደቡብና በምሥራቅ የቻይና ባህር ላይ የቻይና ወታደራዊ ክምች ያሉትንም ነቅፈዋል። በታዳጊ ሀገሮች የምታደርገው ያሉትን የዕዳ ዲፕሎማሲ፣ ሌሎች ሀገሮች ከታይዋን ጋር ያላቸውን ግንኙት እንዲያቋርጡ ለማሳመን ትሞክራለች በማለትም ነቅፈዋታል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ