በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ እና ቬንዙዌላ የእስረኞች ልውውጥ አደረጉ


ኒኮላስ ማዱሮ
ኒኮላስ ማዱሮ

ዩናይትድ ስቴትስ፤ አስራ ይዛ የነበረውን የቬንዌላውን ፕሬዝደንት ኒኮላስ ማዱሮ የቅርብ አጋር ለቃ፣ በምትኩ 10 አሜሪካውያን እስረኞችን እና አንድ ሲፈለግ የነበረ የመከላከያ ሚኒስቴር ተቋራጭን ተረክባለች፡፡

“ፋት ሌናርድ” በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው የመከላከያ ተቋራጭ፣ በፔንታገን ተፈጽሟል የተባለ የጎቦ ቅሌት ዋና ተፈላጊ ሰው እንደነበረ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

በቬንዙዌላ ተይዘው የነበሩት አሜሪካውያን ትናንት ረቡዕ ወደ አገራቸው መግባታቸው ታውቋል።

የእስረኞች ልውውጡ የባይደን አስተዳደር ከነዳጅ አምራቿ አገር ጋር ያለውን ግኑኝነት ለማሻሻል እና ምናልባትም ከማዱሮ አስተዳደር የነዳጅ ማውጣት ፈቃድ ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንደሆነ ተመልክቷል።

ኒኮልስ ማዱሮ፤ የቅርብ አጋራቸው አሌክስ ሳብ በመለቀቃቸው “እውነት አሸናፊ ሆናለች” ብለዋል። “የዲፕሎማቱ አሌክስ ሳብ በሕገ ወጥ መያዝ፣ የአሜሪካ የቅጥፈት ዘመቻ ውጤት ነው” ሲሉ አክለዋል ማዱሮ።

የእስረኞች ልውውጡ የተደረገው፣ የባይደን አስተዳደር በቬንዝዌላ ላይ ተጥለው የነበሩትን የተወሰኑ ማዕቀቦች ባነሳ በሳምንታት ውስጥ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG