በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በዲልታ የኮሮናቫይረስ ዝርያ፣ የሚያዘው ሰው እየጨመረ ነው


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት በሚተላለፈው ዲልታው የኮሮናቫይረስ ዝርያ፣ የሚያዘው ሰው እየጨመረ ነው። ትምህርት ቤቶች እየተከፈቱ ባሉበት ባሁኑ ወቅትም የሚከተቡት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የዋይት ሀውስ የኮቪድ-19 ጉዳይ ከፍተኛ አማካሪዎች አስታወቁ።

የዋይት ሀውስ ዋናው የኮቪድ-19 ምላሽ አስተባባሪ ጄፍ ዜንትስ ትናንት በሰጡት መግለጫ ባለፈው ሀምሌ ወር በሀገሪቱ በቀን የሚከተበው ሰው ብዛት በአማካይ 500 000 እንደነበር ገልጸዋል። ባሁኑ ወቅት ግን በቀን እስከ 900 000 የሚሆኑ እየተከተቡ መሆኑን ነው የገለጹት። ይህ የሆነው አሰሪዎች ለሰራተኞችቻቸው ክትባቱን መከተብ ግዴታ ስላደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

"መከተብን ግዴታ ማድረግ እንደሚሰራ ያሳያል፣ የንግድ ድርጅቶች፣ የጤና ጥበቃ ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ዩኒቨርስቲዎች ፈጥነው በመንቀሳቀስ ይህ ወረርሺኝ እንዲያከትም መርዳት ይኖርባቸዋል" ብለዋል።

የተከታቢዎች ቁጥር በአጭር ጊዜ በዚህ ደረጃ የጨመረው የቫይርሱ ስርጭት በአደገኛ ሁኔታ እያደገ እና በቫይረሱ የሚያዙት ልጆች ቁጥር እጅግ እየጨመረ ባለበት ባሁኑ ውቅት ነው።

በሀገሪቱ ከአስራ ሁለት ዓመት በታች የሆኑ ልጆች ማናቸውንም ጸረ ኮቪድ ክትባት መከተብ አይችሉም። የፌዴራሉ መንግሥት የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር ከአስራ ስድስት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች እንዲሰጥ እስካሁን ሙሉ ፈቃድ የሰጠው ክትባትም የሊለ ሲሆን የፋይዘሩ ክትባት ከ12 እስከ 15 ዓመት ለሆኑ ታዳጊዎች እንዲሰጥ የአጣዳፊ ሁኒታ ፈቃድ ተሰጥቶታል።

XS
SM
MD
LG