በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ ሰላም አስከባሪ ኃይል ከማሊ በጥንቃቄ እንዲወጣ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች


ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፣ ማሊ
ፎቶ ፋይል፦ ባማኮ፣ ማሊ

የማሊ ጊዜያዊ ወታደራዊ ባለሥልጣናት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ኃይል ሃገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ያቀረበው ጥያቄ ያሳዘናት መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በትላንትናው ዕለት ባወጣው በዚህ መግለጫ፡ አወጣጡ “ጥንቃቄ የተመላ እና ሚዛናዊ” ይሆን ዘንድ አሳስቧል።

የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዱላዬ ዲዮፕ፤ አርብ ዕለት የተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በአገሪቱ ባለሥልጣናት እና በመንግስታቱ ድርጅት የማሊ ተልዕኮ መካከል የነበረው እና ለአስር ዓመታት የዘለቀው መተማመን ማሽቆልቆሉን ጠቅሰው ጥያቄውን አቅርበዋል።

የመንግስታቱን ድርጅት የማሊ ተልዕኮ የስምምነት ፈቃድ ለመሻር የአገሪቱ የሽግግር መንግሥት የደረሰበት ውሳኔ አገራቸውን ያሳዘነ መሆኑን የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርቃል አቀባይ ማቲው ሚለር ፤ "ተልዕኮው ኃይሉን ከማሊ በሚያስወጣበት ጊዜ ለሰላምአስከባሪው ሠራዊት አባላት እና ለማሊያውያን ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ እና ከአደጋ በተጠበቀ መልኩ መሆን አለበት፤" ብለዋል።

መግለጫው አያይዞም “ይህ ውሳኔ በማሊህዝብ ፀጥታ እና ከሰብአዊቀውስ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ አሳስቦናል” ብሏል።

ማሊ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2012 ዓም የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ ስር እየሰደደ የመጣውን እስላማዊ አማፂ ቡድን ለመግታትበብርቱ ስትታገል ቆይታለች።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ኃይል የፀጥታውምክር ቤት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2013 ዓም የማሊን መረጋጋትን ወደነበረበት ለመመለስ የተያዙ ጥረቶችን ለመደገፍ በደረሰበት ውሳኔ መሰረት መሰማራቱ ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG