በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ የሥራ አጥ ድጋፍ ጠያቂዎች ቁጥር ቀነሰ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዩናይትድ ስቴትስ የሥራ አጥነት ጥቅማ ጥቅም ጠያቂዎች ቁጥር መቀነሱንና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከመጣ ወዲህ ዝቅተኛው ቁጥር የተመዘገበ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ሥራ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ የተመዘገበው ሳምንታዊው የሥራ አጥነት ድጋፍ ጠያቂዎች ቁጥር 269ሺ ሲሆን ቀደም ሲል ከነበረው ሳምንት በ14ሺ የቀነሰ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ከኮቪድ እያገገመ በሚገኘው የምጣኔ ሀብት እድገት፣ የሥራ አጥ ድጋፍ አመልካቾች ቁጥር እየቀነሰ መመጣቱ የተነገረ ሲሆን፣ እኤአ በ2020 7.1 ሚሊዮን የነበረው ዛሬ ወደ 2.1ሚሊዮን መውረዱ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG