በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ 1ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የሥራ አጥነት ድጎማ ማመልከቻ አስገብተዋል


US-UNEMPLOYMENT
US-UNEMPLOYMENT

የዩናይትድ ስቴትስ የሥራ ሚኒስቴር ዛሬ በገለፀው መሰረት፣ ባለፈው ሳምንት 1ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች፣ የሥራ እጥነት ድጎማ ለማግኘት ማመልከቻ አስገብተዋል። ይህም የአሜሪካ አሰሪዎች፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት፣ ሰራተኞችን ማስወጣት እንደቀጠሉ ያመለክተል ተብሏል።

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ፣ በየሳምንቱ የሥራ አጥነት ማመልከቻ የሚያስቡት ሰዎች ብዛት፣ አንድ ሚሊዮን ገደማ ይሆናል። የቫይረሱ ወረርሽኝ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ከማዳከሙ በፊት ከነበረው፣ በ200,000 ከሚገመት የሥራ አጥነት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ግን፣ የበዛ እንደሆነ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG