በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ጉዳይ በመንግሥታቱ ድርጅት በተሰጠው ድምጽ 'ይበልጥ ሚዛናዊነትን ያንጸባረቀ' ያለችውን የዩናይትድ ስቴትስን አቋም አወደሰች


በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በአስራ አንደኛው የአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ስብሰባ ላይ የተሰጡ የድምጽ ውጤቶች ይታያሉ፡ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም.
በተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በአስራ አንደኛው የአስቸኳይ ልዩ ስብሰባ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ስብሰባ ላይ የተሰጡ የድምጽ ውጤቶች ይታያሉ፡ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም.

ዩናይትድ ስቴትስ "የሰላም መንገድ" በሚል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ባቀረበችው የውሳኔ ሐሳብ ላይ የተሰጠውን ድምጽ ተከትሎ፤ የክሬምሊን ቤተመንግሥት በዩክሬን ጉዳይ "ይበልጥ ሚዛናዊነት የተንጸባረቀበት" ያለውን የዋሽንግተንን አቋም በደስታ መቀበሉን በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ "ለጉዳዩ መቋጫ ለማበጀት (ዩናይትድ ስቴትስ) ያላትን እውነተኛ ፍላጎት" ያሳየ ብለውታል። ብሪታንያ እና ሌሎች የዩናይትድ ስቴትስ አጋር አውሮፓውያን በአንጻሩ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል።

ባለ አራት መስመሩ ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችው ጽሑፍ “በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በተፈጠረው ግጭት” በጠፋው የሰው ሕይወት ያሳደረበትን ሐዘን አስመልክቶ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ዓላማ “ዓለም አቀፍ ሰላምና ደኅንነትን ማስጠበቅ እና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት” መሆኑን ይገልጻል። በተጨማሪም "ግጭቱ በፍጥነት እንዲቆም፤ በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጥብቆ ይማጸናል" ይላል።

"ውሳኔው የሰላም መንገድ የሚያስዘን ይሆናል" ያሉት የዩናይትድ ስቴትሷ የመንግሥታቱ ድርጅት መልዕክተኛ ዶረቲ ሺያ ለምክር ቤት አባላት ሲናገሩ “ይህ የመጀመሪያው፣ ነገር ግን ወሳኙ ርምጃ ነው” ብለዋል። “ሁላችንም ልንኮራበት ይገባል። አሁን ለዩክሬን፣ ለሩሲያ እና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሰላም እና መጭ ጊዜ ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል” ሲሉም አክለዋል።

ውሳኔው ከዩናይትድ ስቴትስ ጋራ ተመሳሳይ ድምፅ የሰጡትን ሩስያ እና ቻይናን ጨምሮ በ10 የድጋፍ ድምጽ ሲጸድቅ፤ ብሪታንያ እናሌሎች አራት አውሮፓውያን የምክር ቤቱ አባል አገራት ድምጽ ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተቃውሞ ድምጽ ያሰማ አባል አገር ግን የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG