በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የጸጥታው ም/ቤት የሰሜን ኮሪያ ሚሳዬሎችን እንዲመክር ጥሪ አቀረበች


ፎቶ ፋይል - እንደ ተንታኞች ገለጻ የሰሜን ኮርያው ህዋሶንግ 12 በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ በኪም ኢል ሱንግ አደባባይ ወታደራዊ ትርኢት ሲደረግ የሚያሳይ ምስል ነው፤ እአአ ኤፕሪል 15/2017
ፎቶ ፋይል - እንደ ተንታኞች ገለጻ የሰሜን ኮርያው ህዋሶንግ 12 በሰሜን ኮሪያ ፒዮንግያንግ በኪም ኢል ሱንግ አደባባይ ወታደራዊ ትርኢት ሲደረግ የሚያሳይ ምስል ነው፤ እአአ ኤፕሪል 15/2017

ዩናይትድ ስቴትስ፣ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት፣ ሰሜን ኮሪያ በቅርብ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስ ይዞታ በሆነቸው የጉዋም ደሴት ይደርሳል በተባለለት የመካከለኛው ርቀት ሚሳዬል ሙክራዋን አስመልክቶ እንዲነጋገር ጥሪ ማቅረቧ ተሰምቷል፡፡

ሰሜን ኮሪያ በጎረቤቶችዋ አገሮች ባላፈው እሁድ የተባለውን ሚሳዬል ሙከራ ማድረጓን አስመልክቶ የተሰራጨውን ዜና በአገሪቱ የመንግሥት ሚዲያ በተለቀቁ ምስሎች አረጋግጣለች፡፡

ዋሶንግ 12 የተባለው የመካከለኛውና ረጅም ርቀት የሚጓዘው የባለሥቲክ ሚሳዬል ሰሜን ኮሪያ እስከዛሬ ከሠራቸው የላቀና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ሊደርስ የሚችል መሆኑን ተነግሮለታል፡፡

የዋይት ሀውስ ባለሥልጣናት የእሁዱ ሙከራዋ የተጣለባትን ማዕቀብ እንዲነሳላት ባለፉት በርካታ ወራት የምታካሂደው ጠብ አጫሪነት ድርጊቶችዋ አካል ነው ሲሉ ገልጸውታል፡፡

XS
SM
MD
LG