በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱ ባይደን ለተመድ ያጩትን አምባሳደር አጸደቀ


ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ እኤአ ጥር 27 2021 በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት
ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ እኤአ ጥር 27 2021 በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት በተባበሩት መንግስታት የዩናይትድ ስቴትስ ቋሚ ልዑክ እንዲሆኑ የታጩትን የነባሯን ዲፕሎማት ሊንዳ ቶማስ ግሪን ፊልድን ሹመት አጽቋል፡፡ በቪኦኤ የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ከፍተኛ ዘጋቢ የሆነችው ሲንዲ ሴይን፣ የቶማስ ግሪንፊልድ ብቃት፣ በዓለም አቀፉ መድረክ እንደ ቻይና ባሉ አገሮች የሚፈተን ይመስላል በማለት፣ የሚከተለውን ዘገባ አሰናድታለች፡፡

አንዳንድ የሪፐብሊካን አባላት ያቀረቡት መጠነኛ ተቃውሞ ምንም እንኳ ሂደቱን ያዘገየው ቢሆንም፣ አምባሰደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ፣ ከሁለቱም የምክር ቤት አባላት 78 ለ20 በሆነ ድምጽ ከፍተኛ ድጋፍ አግኘተዋል፡፡ ትናንት ማክሰኞ በተባበሩት መንግሥታት ወኪልነት የታጩትን የዲፕሎማቷን ሹመት ለማጽደቅ 20 የሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላት ከዴሞክራቶቹ ጋር አብረዋል፡፡

ባለፈው ወር የዲፕሎማቷን ሹመት ለማጽደቅ በነበረው የክርክር ሂደት አንዳንድ ምክር ቤት አባላት ቶማስ ግሪንፊልድ በኮሚኒስቱ የቻይና መንግሥት ላይ ያላቸው አቋም የተለሳለሰ ሊሆን ይችላል የሚል ቅሬታ አስነስቶ ነበር፡፡ ለተባበሩት መንግሥታት አምባሳደርነት የታጩት ዲሎማቷ ሊንዳ ግሪን ፊልድ ግን ለቻይና የተመቸነው ከሁሉም ቦታ እየለቀቀች በመውጣታችን ነው በማለት ይህን ብለዋል

“በተለይ ቻይና የተባበሩት መንግሥታትን ተቋማት ሁሉ በመጠቀም ከአሜሪካ ተቋማትና እሴቶች ተቃራኒ በሆነ መንገድ የራሷን አምባገነን አጀንዳ ማራመድ ተጠቀምበታለች፡፡ ይህ ደግሞ የሆነው እኛ ከሁሉም ቦታ እየለቀቅን በመውጣታችን ነው፡፡ ካሁን በኋላ እኔ በኃላፊነት ላይ እስካለሁ ድረስ፣ ይህ አይደገምም፡፡ “

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:39 0:00


ይህንን አባባል በመደገፍ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ትናንት ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ፣ ቻይና በዓለም ላይ የምታደርገውን ነገር ሁሉ ለመመከት ጥንካሬ የሚሰጠን፣ የአሜሪካ እሴቶች እና የዩናይትድ ስቴትስ አጋሮች ትብብር ነው ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ አያይዘውም “ቻይናን ለብቻችን መግጠም ስንፈልግ ልክ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው፣ በተለይ በበጋራና ሁሉንም አስተባብረን ከምናገኘው አንጻር ሲስተያይ ውጤቱ እጅግ አነስተኛ ነው፡፡”

ቶማስ ግሪንፍ ፊልድ በ35 ዓመት የዲፕሎማት አገልግሎታቸው በዲሞክራትና ሪፐብሊካን አሳተዳደሮች ውስጥ በመስራት የተካባተ ልምድ አላቸው፡፡ በአፍሪካ ጉዳዮች ባላቸው ልዩ እውቀት በላይቤሪያ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በኬንያ ጋምቢያ እና ናይጄሪያም ውስጥ በኃላፊነት ሠርተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG