የዩክሬይን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬይንን ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ማዕድኖች እንድታገኝ የሚያስችል ስምምነት ለመፈረም፣ ነገ ዐርብ ወደ ኋይት ሐውስ ይመጣሉ፤ ሲሉ፣ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ተናገሩ፡፡
"የዩክሬይን ፕሬዝደንት፣ ነገ ዐርብ ይመጣሉ፤ የማዕድን ስምምነቱን እንፈርማለን፤" ብለዋል ትረምፕ።
የዩክሬይኑ ፕሬዝደንት በበኩላቸው፣ አኹንም ያልተፈቱ ጥቂት ጉዳዮች እንዳሉ አመልክተዋል።
ስምምነቱ፣ ዩክሬይን የሩሲያን ወረራ ለመመከት ላለፉት ሦስት ዓመታት እያካሔደች ባለችው ውጊያ፣ ዋሽንግተን ለላከችላት የጦር መሣሪያ ካሳ እንዲኾን፣ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውንና በቀላሉ የማይገኙ የዩክሬይን ማዕድኖችን እንድታገኝ ከፍተኛ መብት እንደሚሰጣት ተመልክቷል፡፡
የቪኦኤ የኋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም