በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ የሚሳዬል ጥቃት ሰባት ሰዎች ተገደሉ 28 ቆሰሉ


የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ

የዩክሬን ባለስልጣናት በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ከተማ ትላንት ሐሙስ በደረሱ የሩስያ ጥቃቶች “ቢያንስ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል በትንሹ 28 ሰዎች ቆስለዋል” ሲሉ ተናገሩ፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ጥቃቱ “እጅግ ጭካኔ የተሞላበት ነው” ብለዋል።

"ከዛሬው የሩሲያ ኢላማዎች መካከል የዩክሬን ትልቁ የህትመት ተቋም አንዱ ነበር።” ያሉት ዜለነስኪ “የሚሳዬል ጥቃቱ ብዙ ሰዎችን ገደሏል፣ አቁስሏል ። የመጽሃፍ ማከማቻ እና ቁሳቁሶች በእሳት ወድመዋል” ብለዋል፡፡

ብዙ የዩክሬን አታሚዎች መጽሃፎቻቸውን እዚያ ማሳተማቸውን ዜለነስኪ ገልጸው “ይህ የሩሲያ ኢላማ ነው። አሸባሪዎች ሁሉንም የሕይወት ዘርፎች ማቃጠል እና ማጥፋት ይፈልጋሉ።” ብለዋል፡፡

በካርኪቭ ክልል አገረ ገዥ እንደተናገሩት ካርኪቭ የተመታችው በዘጠኝ ሮኬቶች ነው፡፡ በተለያዩ ቦታዎች በደረሰው በዚህ ጥቃት ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 11 መቁሰላቸውን ባለሥልጣኑ ተናግረዋል፡፡

ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ነዋሪዎች ያሏት ካርኪቭ ፣ ከሩሲያ ድንበር 19 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን እስካሁን 15 ጊዜ ያህል በሩሲያ ሚሳዬሎች መደብደቧን ባለሥልጣኖች ይናገራሉ፡፡

ዜለንስኪ እንዲህ ያሉ የሚሳዬል ጥቃቶችን የሚከላከሉበትን መሳሪያዎች ከምዕራባውያን አጋሮች ባለማግኘታቸው የተሰማቸውን ቅሬት ገልጸዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ275 ሚሊዮን ዶላር ወታደራዊ ዕርዳታ እያዘጋጀች መሆኑን በርካታ ባለሥልጣናት ለሮይተርስ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG