አዲስ አበባ —
በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ፣ የላቲን አሜሪካና የካሪቢያን ሃገሮች ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላም እያደረገ ነው ያሉትን ጥረትና ሠራዊቱን ወደ ትግራይ አዝልቆ ላለማስገባት መወሰኑን አድንቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሞሊ ፊ እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዴቪድ ዞተርፊልድ በወቅታዊው የሃገሪቱ ጉዳዮች ላይ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ለመነጋገር አዲስ አበባ እንደሚገኙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት አስታውቋል።