ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቅርቡ ከየመን ሁቲዎች የሚደርስባት የሚሳዬል ጥቃቶችን ለመመከት የሚያስችላት የሚሳዬል አውዳሚ መሳሪያዎችና የጦር ጀቶችን እየላከች መሆኑን ተገለጠ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ስለመሣሪያዎቹ ከአቡዳቢ መሀሙድ ቢን ዛይድ አል ናሃያን ጋር ትናንት ማክሰኞ በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡
እኤአ ባላፈው ጥር 17 አቡዳቢ በሚገኘው አንድ የነዳጅ ተቋም ላይ በአማጽያኑ በተሰነዘረ ጥቃት ሦስት የውጭ አገር ሠራተኞች መገደላቸው ይታወሳል፡፡