ዋሺንግተን ዲሲ —
የረጅም ርቀት የሚሳይል መከላከያው ከመዲናዋ አንካራ ወጣ ብሎ የሚገኘው የአየር ኃይል ሰፈር ገብቷል።
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት አባል ሃገር ከሩስያ ጋር የጦር መሳሪያ ግዢ ስትዋዋል የቱርኩ የመጀመሪያ ሲሆን፣ ያቺ ሃገር ወደሞስኮ ቀረብ እያለች ነው የሚል ጥርጣሬ ተቀስቅሷል።
ዩናይትድ ስቴትስ ቱርክ ይህን ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ የተገመተ የመሳሪያ ግዢ ውል እንድትሰርዝ ስትወተውት ቆይታለች። የጦር መሳሪያ ግዢ ውሉ አንካራን ለማዕቀብ እንደሚያጋልጣት እና ኤፍ 35 ተዋጊ ጀቶች ለመገንባት ከተደራጀው ስብስብ አስወጥቶ ለብዙ ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ሊዳርጋት እንደሚችል ዩናይትድ ስቴትስ ስታስጠነቅቅ ቆይታለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ