በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ ስለሚጣለው ታሪፍ አስፈላጊነት ማስረዳቱን ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል፡ ዶናልድ ትረምፕ ከካናዳው ጠቅላይ ምኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር
ፎቶ ፋይል፡ ዶናልድ ትረምፕ ከካናዳው ጠቅላይ ምኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋር

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ቻይና እና ሜክሲኮ ላይ ለምን ታሪፍ መጣል አስፈላጊ እንደሆነ በሳምቱ መጨረሻም ክርክሩን ማቅረብ ቀጥሎ ነበር። ሶስቱ ሃገራት የአጸፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀው፣ ነገር ግን ከአሜሪካ ጋር ለመነጋገርና ለመተባበር በራቸው ክፍት እንደሆነ ገልጸዋል።

ዛሬ ጠዋት ላይ ደግሞ ዶናልድ ትረምፕ ከካናዳው ጠቅላይ ምኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ጋራ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።

የትረምፕ አስተዳደር በካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይና ላይ ስለሚጣለው ታሪፍ አስፈላጊነት ማስረዳቱን ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:58 0:00

ዶናልድ ትረምፕ “ትሩዝ ሶሻል” በተወሰኘው ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ እኩለ ቀን ላይም ከትሩዶ ጋራ ለመነጋገር ቀጠሮ እንደያዙ አስታውቀው፣ አዲስ ታሪፍ በካናዳ ላይ የጣሉት በአሜሪካ የበርካቶችን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ የሚገኘውን ፈንትነል የተሰኘው ሱስ አሲያዥ መድሃኒት በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ መግባቱን ለመከላከል ካናዳ ተጨማሪ ጥረት እንድታደርግ ጫና ለመፍጠር መሆኑን አስታውቀዋል። ትረምፕ በተጨማሪም ከሜክሲኮ ፕሬዝደንት ክላውዲያ ሼይንባውም ጋራ ለመነጋገር ዕቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

ቬሮኒካ ባልዴራስ ኤግሌሲያስ የላከችው ዘገባ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG