በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ለከፍተኛ ዳኝነት ውሳኔ ያቀረቧቸው ስው ጉዳይ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለከፍተኛ ዳኝነት ውሳኔ ያቀረቧቸው ስው ጉዳይ በሌላ የፖለቲካ ትርዒት ምክንያት የሀገሪቱ ምክትል ዋና አቃቤ ህግ ጉዳይ መቆየቱ አልቀረም። ሮድ ሮዘንስቴን ሩስያ ካች አማና በተካሄደው የአሜሪካ ምርጫ ውስጥ ጣልቃ ስለመግባቷ ጉዳይ የሚካሄደውን ልዩ ምርመራ በበላይነት ይመራሉ።

ትረምፕና ሮዘንስቴን ባለፈው ሳምንት ኒው ዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ላይ ስለወጣው ዘገባ ዛሬ ተገናኝተው እንዲነጋገሩ ነበር የታቀደው። የፕሬዚዳንቱ አማካሪ ኬሊአን ኮንዌ የሁለቱ ሰዎች ስብሰባ ሊዘገይ እንደሚችል “ፎክስ ኤን ፍሬንድስ” ለተባለው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል። በዘገባው መሰረት ፕሬዚዳንቱ የሥራ ብቃት የላቸውም ተብለው ከሥልጣን ለማንሳት ማስረጃ እንዲሆን ሮዘንቴን ትረምፕን በድብቅ የመቅረፅ ሃሳብ አቅርበው ነበር።

ምክትል ዋናው አቃቤ ህጉ በበኩላቸው ይህን አላደረግኩም። ሀሰት ነው የሚሉ ሁለት መግለጫዎች አውጥተዋል።

ይሁንና የህግ መምሪያው ምክር ቤት የፍርድ ጉዳይ ኮሚቴ የዳኛ ብሬት ካቫኖንና የዶ/ር ክርስቲን ብሌዚ ፎርድን ጉዳይ ስለሚያዳምጥ የሮዘንስቴን ጉዳይ እንዲዘገይ ተደርጓል።

ዶ/ር ፎርድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያሉ አሁን ለከፍተኛ ዳኛነት የተሰየሙት ካቫኖ ሊደፍሩኝ ሞክረው ነበር የሚል ክስ ማቅረባቸው የሚታወቅ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG