በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ በፖለቲካው ዓለም መቀጠል ፓርቲያቸውን እያነጋገረ ነው


የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በፍሎረንስ፣ አሪዞና በተካሄደው ሰልፍ ላይ ንግግር አድርገዋል፣ እኤአ ጥር 15 ቀን/2022
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በፍሎረንስ፣ አሪዞና በተካሄደው ሰልፍ ላይ ንግግር አድርገዋል፣ እኤአ ጥር 15 ቀን/2022

የቀደሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ወደ 15ሺ ለሚደርሱ ጠንካራ ደጋፊዎቻቸው አሪዞና ውስጥ የቅስቀሳ ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡

ደጋፊዎቻቸው በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ወይም ካፒቶል ላይ እኤአ ጥር 6 ያደረሱት ጥቃት አንደኛ ዓመቱ ከተከበረ ወዲህ ትረምፕ በአደባባይ ያደረጉት የመጀመሪያው ንግግራቸው ነው ተብሏል፡፡

93 ደቂቃ ፈጅቷል በተባለው በዚህ ንግግራቸው ትረፕም ከዚህ በፊት የምርጫው ውጤት ተሰርቋል በማለት ያሰሙትን የሀሰት ክስ በድጋሚ የገፉበት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ትረምፕ እኤአ በ2024 በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሪፐብሊካን ድል እንደሚቀናቸው ተናግረዋል፡፡

አንዳንዶቹ ተንታኞች የፕሬዚዳንቱ ንግግር ትራምፕ ወደ ዋይት ሀውስ ለመመለስ ፍላጎት ያላቸው መሆኑን ፍንጭ ያሳዩበት ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ትረምፕ በቀጣዮቹ ወራት በርካታ የቅስቀሳ ዘመቻ መድረኮችን እንደሚያዘጋጁም ተመልክቷል፡፡

በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶችን ለመቆጣጠር በሚደረገው በህዳር ወሩ ምርጫና በፕሬዚዳንት ባይደን የመጀመሪያው ዙር ስልጣን ፍጻሜ አካባቢ በርካታ ቅስቀሳዎችን እንደሚያደርጉ ተገምቷል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ደጋፊዎቻቸው፣ ትራምፕ ለረጅም ጊዜ በአሜሪካ የፕሬዚዳንት ፖለቲካ ውስጥ የሚቆዩ ሲሆን “የባይደን ድክመትና ውድቀት የትራምፕን ትክክለኝነት እያረጋገጠልን ነው” ብለዋል፡፡

አብዛኞቹ መከካለኛውን መንገድ የያዙ የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት፣ የትረምፕ ወደ ፖለቲካ መመለስ ለአገሪቱም ሆነ ለሪፐብሊካን ፓርቲ ጥሩ አለመሆኑን እያነሱ ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG